Fana: At a Speed of Life!

እንደአሁኑ አማራጭ ዕድል ቢኖር ኖሮ ወደ ትጥቅ ትግል አልገባም ነበር – አምባሳደር ሌንጮ ባቲ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) አዲሱ መንግሥት አሁን እንደጀመረው አካታችና አማራጭ የፖለቲካ አካሄድ ቢኖር ኖሮ ወደ ትጥቅ ትግል አልገባም ነበር ሲሉ የቀድሞ የኦነግ አመራር አባልና በሳውዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት ሌንጮ ባቲ ተናገሩ።
አምባሳደር ሌንጮ ባቲ እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ በተዛነፈና በአግላይ የፖለቲካ አስተሳሰብ ምክንያት በቅራኔ ውስጥ ዘመናትን እንድታሳልፍ ተገዳ ኖራለች።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ የለውጥ ጥማት ነው ያሉት አምባሳደር ሌንጮ ÷ እኩልነት እና ወንድማማችነት እንዲሰፍን ብሎም ተፎካካሪ ፓርቲዎች እንደ ጠላት ሳይሆን እንደ አንድ የሀገሪቱ ባለድርሻ አካል እንዲታዩ የሚሰራ ባለራዕይ መሪ ማግኘት የህዝቡ ጥያቄ እንደ ነበርም ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ ምኞታቸው እውን መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት።
አክለውም ከ60ዎቹ ጀምሮ እስከ ኢህአዴግ ዘመነ መንግሥት ማብቂያ ድረስ በሀገሪቱ እንደ ቡድንም ሆነ እንደ ግለሰብ የፖለቲካ ተሳትፎ ያደረጉና የመብት ጥያቄ ያነገቡ አያሌ ወጣቶችና ምሁራን ሕይወታቸውን ጭምር በመገበር ዋጋ መክፈላቸውን አውስተዋል።
በሕዝብ መራራ ትግል ወደ ሥልጣን የመጣው የለውጥ አመራርና አሁን የተመሰረተው አዲሱ መንግስት ለሕዝብ ጥያቄዎች ተገቢውን ክብር በመስጠትና የተለያዩ አስተሳሰቦች እንዲንሸራሸሩ በማድረግ ከሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለመስራት የሚያደርገው ጥረት የሚያስመሰግነው ተግባር ነው ሲሉ መግለጻቸውን የኢፕድ ዘገባ አመላክቷል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.