Fana: At a Speed of Life!

እንደ ሸረሪት ግድግዳ የሚወጣው ህንዳዊ ህጻን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ነገሩ በህንድ ፕራዳሽ ግዛት የተፈጸመ ነው፡፡ የሰባት ዓመቱ ህጻን ያሻርዝ ጉኣር አንድ ለየት ያለ ነገር በመሞከር አለምን አስገርሟል፡፡ ጉኣር የሦስተኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን ካናፑር በምትባል ከተማ ውስጥ ከቤተሰቦቹ ጋር ነው የሚኖረው፡፡

ጉኣር በአንድ ዕለት በፊልሙ ዓለም ታዊቅ ከሚባሉት ውስጥ ስፓይደር ማን የተሰኘውን ይመለከታል፡፡

ስፓይደር ማን የሱፐርሄሮ ወይንም የጀግንነት ገጸ ባህሪን በመላበስ ከሚጫወቱ ዝነኛ ፊልሞች መካከል የሚመደብ ነው፡፡

ስፓይደር ማን ጋራው ሸንተረሩ የማይገድበው ግድግዳውን እንደሸረሪት መውጣት የሚችል ለየት ያለ ገጸ ባህሪ ነው፡፡

ይህንን የተመለከተው የሰባት ዓመቱ ህንዳዊውም ፊልሙን እንዳየሁት ግድግዳውን መውጣት ፈለግሁ ይላል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ እንደስፓይደር ለመሆን ሲሞክር መውደቁን ይናገራል፡፡

በዚህ ተስፋ ያልቆረጠው ጉኣር በየዕለቱ ልምምዱን ቀጠለ፡፡

በልምምዱ መካከል አንድ ቀን ግድግዳውን የወጣው ጉኣር  ቤተሰቦቹን ጠርቶ እንዳስገረማቸው ተናግሯል፡፡

ጉኣር ከሦስት ሜትር በላይ የሆነውን የቤተሰቡን ልሙጥ የሆነ ግድግዳ የሚወጣው እጆቹንና እግሮቹን በመጠቀም ብቻ መሆኑ ምስሎቹ ያሳያሉ፡፡

ግድግዳ መውጣቱን የተመለከቱ ቤተሰቦቹ እንደተገረሙ ከተናገረ በኋላ ‘’እንዳልወድቅ ስጋት ገብቷቸው ነበር’’ ይላል፡፡

ቀስ እያለም ጎረቤት የአካባቢው ሰው ችሎታውን እየሰማ ከሄደ በኋላ በከተማው ዝናው መናኘቱን ኦዲቲይ ዘግቧል፡፡

ተንቀሳቃሽ ምስሉ ከታች ይገኛል፡-

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.