Fana: At a Speed of Life!

እንግሊዝ ከታንዛኒያ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚገቡ ተጓዦች ላይ እገዳ ጣለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እንግሊዝ ከታንዛኒያ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚመጡ ተጓዦች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ እገዳ ጣለች፡፡

እገዳው በደቡብ አፍሪካ የታየው አዲሱ የኮቪድ -19 እንዳይስፋፋ በማሰብ የተጣለ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ከዛሬ ጀምሮ ከታንዛኒያ እና ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንገደኞችን ማገዷን የሃገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ጸሐፊ ግራንት ሻፕስ ተናግረዋል፡፡

በተያያዘም በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከሌሎች 11 ደቡብዊ የአፍሪካ ሃገራት የመጡ ተሳፋሪዎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ወደ እንግሊዝ እንዳይገቡ መታገዳቸው ታውቋል፡፡

የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል ባወጣው መረጃ የአህጉሪቱ የኮቪድ -19 ሞት መጠን አሁን ዓለም ላይ ካለው አማካይ 2 ነጥብ 2 በመቶ ከፍ ብሎ 2 ነጥብ 5 በመቶ መሆኑን ገልጿል፡፡

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደግሞ ከ21 የአፍሪካ ሃገራት መካከል የሞት መጠን ከ3 በመቶ በላይ ደርሷል ነው የተባለው ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.