Fana: At a Speed of Life!

እንግሊዝ ከፈረንሳይ እና ከኔዘርላንድስ የሚገቡ ሰዎችን ለ14 ቀናት ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ልታስገድድ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) እንግሊዝ ከፈረንሳይ እና ከኔዘርላንድስ የሚገቡ ሰዎችን ለ14 ቀናት ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ልታስገድድ ነው፡፡
ሃገሪቱ ይህን የምታደርገው ከነገ ጀምሮ መሆኑን አስታውቃለች፡፡
ራሳቸውን የማያገሉ ሰዎች ላይም ቅጣት እንደምትጥል ገልጻለች፡፡
ይህ መመሪያ ከፈረንሳይ በተጨማሪ ማልታ፣ ቱርክ እና አሩባ በሚገቡ መንገደኞች ላይም ተግባራዊ ይሆናል ነው የተባለው፡፡
ይህን ተከትሎም ፈረንሳይ የእንግሊዝ ውሳኔ ወደ አጸፋዊ እርምጃ ሊወስዳት እንደሚችል ገልፃለች፡፡
ከፈረንሳይ በተጨማሪም ማልታ ከእንግሊዝ የሚገቡ መንገደኞች ላይ የ14 ቀን ለይቶ ማቆያን ተግባራዊ አደርጋለሁ ብላለች፡፡
አሁን ላይ በእንግሊዝ 313 ሺህ 798 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን 4 ሺህ 347 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.