Fana: At a Speed of Life!

እውቁ ኬንያዊ አትሌት ፖል ቴርጋት ሀዋሳ ከተማ ገባ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እውቁ የኬንያ አትሌት ፖል ቴርጋት የኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣቶች የኦሎምፒክ ውድድርን ለመታደም ሀዋሳ ከተማ ገብቷል፡፡

አትሌት ፖል ቴርጋት በሲዳማ ክልል አዘጋጂነት ከግንቦት 21 እስከ ሰኔ 4/2014 ዓ.ም ድረስ የሚካሄደውን 1ኛውን የኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣቶች የኦሎምፒክ ውድድርን በክብር እንግድነት ለመታደም ነው ሀዋሳ ከተማ የገባው፡፡

በተጨማሪም የአፍሪካ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ አቶ አህመድ ጋሽም፣ የብሩንዲ ኦሎምፒክ ፕሬዚዳንትና የአፍርካ ኦሎምፒክ ሥራ አስፈፃሚ፣ የኬንያ ኦሎምፒክ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ዞን 5 ዋና ጸሐፊ፣ ዶክተር ቶኒ የደቡብ ሱዳን የኦሎምክ ፕሬዝዳንት፣ አቶ ልዑል ፍሰሃ የኤርትራ ኦሎምፒክ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ዞን 05 ዓቃቤ ንዋይ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም ሀዋሳ ገብተዋል።

በተመሳሳይ የኦሎምፒክ ውድድሩን ለመታደም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፌጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ሀዋሳ ከተማ መግባታቸው ታውቋል፡፡

እንግዶቹ ሀዋሳ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንትና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ፥ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ጋር በመሆን አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።።

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣቶች የኦሎምፒክ ውድድር በነገው ዕለት በሲዳማ ክልል አዘጋጅነት በሀዋሳ ከተማ ይጀመራል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.