Fana: At a Speed of Life!

እየተደረገ ባለው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ግምገማ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸው ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉባ እየተደረገ ባለው የ100 ቀናት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ግምገማ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸው ተጠቁሟል።

በዚህም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የማዕድን ሚኒስቴር እና ፍትህ ሚኒስቴር በተያዘው እቅድ መሰረት ስራዎች መሰራታቸውን ሚኒስትሮቻቸው ተናግረዋል።

ግምገማው በህዳሴ ግድብ መገኛ ጉባ ላይ መደረጉም የራሱ የሆነ ልዩ ስሜት እንደፈጠረላቸውም ጠቁመዋል፡፡

የሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የ100 ቀናት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ በህዳሴ ግድብ መገኛ በሆነው ጉባ ከትናንት ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

በዓላዛር ታደለ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.