Fana: At a Speed of Life!

እጅን በሚገባ በመታጠብ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በአግባቡ በመጠቀም ኮሮናን መከላከል ይገባል – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ሐሌ 25 ፡ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እጅን በሚገባ በመታጠብ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በአግባቡ በመጠቀም ኮሮናን መከላከል እንደሚገባ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገር ደረጃ ኮቪድ19ን የመከላከል እርምጃዎችን ቀደም ብለን መጀመራችንን አስታውሰዋል፡፡

የነበረው የጋራ ጥረት ውጤታማ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቫይረሱን የመከላከል ስራው ቀደም ብሎ መጀመሩ መሰላቸትን ያስከተለ ይመስላል ብለዋል።

ባለፉት ሁለት ሳምንታትም ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ መሰራጨቱን ጠቅሰው ይህም መዘናጋት እና ቸልታን ማስወገድ እንደሚገባ ማሳሳቢያ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ከዚህ አንጻርም እጅን በሚገባ በመታጠብ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በአግባቡ በመጠቀም እንዲሁም ዘወትር ርቀትን በመጠበቅ ቫይረሱን መከላከል እንደሚገባ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.