Fana: At a Speed of Life!

እግረ ረጅሟ የዓለማችን ታዳጊ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካዊቷ የ17 ኣመት ታዳጊ 4 ጫማ በሚረዝመው ረጅሙ እግሯ ሁለት ጊዜ ስሟን በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገቦች ማስፈር ችላለች።

ማሲ ኩሪን የተባለችው የቴክሳስ ነዋሪዋ ታዳጊ ግራ እግር 5 ነጥብ 25 ኢንች ርዝመት ያለው ሲሆን ቀኝ እግሯ ደግሞ 4 ነጥብ 87 ኢንች ርዝመት አለው ተብሏል ፡፡

በዚህም የ17 ዓመቷ ኩሪን በሴት የዓለም ረዥም እግሮች ባለቤትና የረጃጅም እግሮች እንዳሏት በጊነስ መዝገብ መረጋገጡ ተገልጿል፡፡

የኩሪን ቤተሰቦች ረጃጅሞች ሲሆኑ ከዘመዶቿ መካከል እርሷ ካላት ስድስት ጫማ ከ10 ኢንች ቁመት ጋር የሚመሳሰል እንደሌለ ተናግራለች ፡፡

ታዳጊዋ አክላም አንድ ቀን ረጅሟ ሞዴል የመሆን እቅድ እንዳላት ተናግራለች።

ምንጭ፡-upi.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.