Fana: At a Speed of Life!

ኦማር ሃሰን አልበሽር ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው ሊሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን የሽግግር መንግስት የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽርን ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፎ ሊሰጥ መሆኑ ተሰምቷል።

ኦማር አልበሽር በሀገሪቱ በፈረንጆቹ 2003 በተቀሰቀሰው የዳርፉር ግጭት ወቅት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ሲወነጀሉ ቆይተዋል።

በወቅቱ በዳርፉር በመንግስት ደጋፊዎችና በአማጽያን በተፈጠረው ግጭት 300 ሺህ ሰዎች መሞታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት መረጃ ያመላክታል።

ከዚህ ባለፈም 2 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።

ይህን ተከትሎም ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አልበሽር ፈጽመውታል ባለው የዘር ማጥፋት፣ የጦር ወንጀለኝነት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲያዙ ማዘዣ ማውጣቱም ይታወሳል።

አሁን ላይም የሱዳን የሽግግር መንግሥቱ ኦማር አልበሽር ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፎ ሊሰጥ መሆኑን የሀገሪቱ ወታደራዊ ምክር ቤት አስታውቋል።

ምንጭ ፥ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.