Fana: At a Speed of Life!

ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሲያካሂድ የቆየው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ እክል ገጠመው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሲያካሂድ የቆየው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ እክል እንደገጠመው አስታወቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ሙከራዎቹን በስኬት ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡

ይህንንም ተከትሎ ኦክስፎርድ ከአስትራዜኒካ ጋር በመሆን ወደ ሶስተኛውና መጨረሻ የሙከራ ደረጃ ተሸጋሯል፡፡

ሆኖም በሶስተኛ ደረጃ ሙከራው እንዳረጋገጠው ፍቃደኛ ተሳታፊዎች ህመም እንደገጠማቸው ነው የገለጸው፡፡

በዚህ ምንነቱን እስከ አሁን ባልገለጹት ህመም ምክንያት ሙከራውን ማዘግየታቸውን ነው ያሳወቁት፡፡

የክትባቱ ሙከራ እክል ሲገጥመው ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ተነግሯል፡፡

እስከ አሁን ድረስ ከአሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ የተውጣጡ 30 ሺህ ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ቃል አቀባይ እንደዚህ ዓይነት ሰፊ ሙከራዎች ሲካሄዱ ህመም ሊያጋጥም እንደሚችል ገልጸው ነገር ግን በጥንቃቄ አካሄዶ መመርመር ይገባል ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ቃልአቀባዩ ሙከራው ዳግም በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚጀመርም ተስፋ ሰጥተዋል፡፡

ይህ በዓለም ዙሪያ ተስፋ ከተጣለባቸው የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች መካከል ዋነኛው እንደነበር ይነገራል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም ዙሪያ 180 የሚደርሱ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች ሙከራ ላይ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.