Fana: At a Speed of Life!

ከሀዲውን ኮሎኔል በቁጥጥር ስር ያዋለችው ጀግናዋ ም/አስር አለቃ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 20ኛ ቃሉ ክፍለ ጦር ሰሜን ዕዝ ካሏት የጦር ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው።

በዚህ ክፍለ ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል የሆነችው ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባልቄ የሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ አጃቢ ነች ። ጁንታ መሆኑን ግን አታውቅም ።

የእብሪት እርምጃቸው ከመጀመሩ ከ3 ቀናት በፊት ሰራዊቱ የምግብና መጠጥ አገልግሎት የሚያገኝባቸውን መንገድ በመዝጋት ሰራዊቱን ለከፍተኛ ርሃብና ጥም ዳርጏል ።

ሁሉም የሰራዊት አባል የግል ትጥቁን በአንድ ክፍል በማስቀመጥ በህብረተሰብ የድጋፍ ስራዎች ላይ እንዲረባረብ ማድረጉን ትናገራለች ።

በተለይም ጥቅምት 24 ቀን 2013 ምሽት ላይ ሁሉንም የጥበቃ ቦታዎች በትግራይ ተወላጅ የሰራዊት አባላት እንዲሸፈኑ በማድረግ ፣ የከሃዲው ቡድን ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ምንም አይነት ዝግጅትና ትጥቅ ባልነበረው ሰራዊቱ ላይ ከፍተኛ ተኩስ እንዲከፍትም አድርጏል ብላለች ።

ሆኖም ታላቅ ጀግንነትና ኢትዮጵያዊ ማንነትን የወረሰው ጀግናው ሰራዊት የማይታሰቡ ጀብዶችን ጭምር በመፈፀም ፣ ወደ ኤርትራ ስልታዊ ማፈግፈግ በማድረግ ራሱን ማዳን እንደቻለ ትገልፃለች።

በዚህ ሁሉ ግፍና በደል መሃል የሻለቃዋ ዋና አዛዥና ለዘመናት የመራቸውን የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የካደው ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ ራሱን መፀዳጃ ቤት ውስጥ በመደበቅ በጁንታው የተሰጠውን ተልዕኮ መፈፀም እንደጀመረ በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆና አስታውሳለች ።

ውትድርና በኢትዮጵያዊነት ፍቅር መታጠብና በጀግንነት ካባ መድመቅ ነው የምትለው እንስቷ ጀግና ፣ ራስህን ለሃገር አሳልፈህ ከሰጠህ ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻውን ጀግንነትን ይወልዳል ስትል የቀድሞ አለቃዋን እንዴት ከስሯ እንዲንበረከክ እንዳደረገችው እንዲህ ታጫውተናለች ።

“… ሰራዊጹን በታፈነበት ጥቅምት 24 ምሽት 2 ሰዓት ላይ በከባድ መሳሪያ የታጀበ ተኩስ ወደ ካምፕ ተተኮሰ፣ በዚህ ሰዓት ወደ  መፀዳጃ ቤት ራሱን የደበቀው ከሃዲው አዛዥ ተብዬ ፣ እኔ በትግራይ ሚሊሻና ልዩ ሃይል ጥይት ከምሞት አንተን ገድዬ ራሴን አጠፋለሁ አልኩት፣ ተኩሱ በርትቷል፣ ሁሉም ራሱን ለማዳን ወደህሊናው የመጣለትን አማራጭ እየተጠቀመ ይሯሯጣል…” ስትል ታስታውሳለች።

“… በመጨረሻም ከተደበቀበት መፀዳጃ ቤት እንዲወጣና እኔ የምለውን ብቻ እንዲፈፅም እሽ የማይል ከሆነ ግን እንደምገድለው አስጠነቀቁት፥ እሱም በፍርሃት ውስጥ ሆኖ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ ወደነገርኩት ቦታ መጣ፥ ሽጉጡንና ማዕረጉን እንዲሰጠኝ አደረኩ፣ ከዛም ጫማውን እንዲያወልቅ አድርጌ በየመንገዱ ከማገኛቸው የሰራዊት አባላት ጋር በመተባበርና ሙሉ ለሊት የእግር ጉዞ በማድረግ ኤርትራ ይዤው በመግባት ታማኝ እና ሙሉ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ አመራሮች አስረከብኩ ።”

ሰራዊታችን በራሱ ወገኖች የደረሰበትን በቃላት የማይገለፅ ግፍና በደል ተሸክሞ ቂምን ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ፍቅር አስቀድሞ ለድል በመብቃቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማትም ምክትል አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ  ለመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገፅ ገልፃለች።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.