Fana: At a Speed of Life!

ከሃዲው የህወሓት ቡድንን ለማስወገድ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን እንሰለፋለን – የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ከሀዲውን የህወሀት ቡድን ለማስወገድ ለሀገር መከታ ከሆነው የመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፍ እንደሚደግፉ በደቡብ ኦሞ ዞን የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

ነዋሪዎቹ ድጋፋቸውን የገለጹት በጂንካ ከተማ እያካሄዱ ባሉት ሰላማዊ ሰልፍ ባሰሟቸው መፈክሮች ነው።

ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በመደገፍና የከሀዲውን የህወሓት ቡድን በማውገዝ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።

የጦር መሳሪያ ከትግራይ ህፃናት ትከሻ ላይ ይውረድ፣ ለትግራይ ህፃናት እስክሪብቶ እንጂ መሣሪያ አይገባቸውም፣ብሔራዊ ጥቅማችን እና ሉዓላዊነታችን ይከበር፣ ፈተናዎችን እየመከትን የተስፋ ብርሃን ለማድመቅ እንሰራለን፣ የአድሎ እጃችሁን ከኢትዮጵያ አንሱ የሚሉ ሰልፈኞቹ ካሰሟቸው መፈክሮች መካከል የተመለከቱ ናቸው።

ሰልፈኞቹ፥ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ሊበትን የተነሳውን ከሃዲ የጁንታው ቡድንን ለማስወገድ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።

ወጣቶችና ሴቶችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰልፉ እየተሳተፉ እንደሚገኙ የዘገበው ኢዜአ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.