Fana: At a Speed of Life!

ከላም ቆዳ በእጅ የተዘጋጀው የዓለማችን ትልቁ መጽሃፍ ለእይታ በቅቷል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከላም ቆዳ በእጅ የተዘጋጀው የዓለማችን ትልቁ መጽሃፍ ለእይታ በቅቷል።

በሃንጋሪ ገጠራማ አካባቢ የተዘጋጀው መጽሃፍ ባህላዊ መንገዶችን ብቻ በመጠቀም የተሰራ ነው ተብሏል።

መጽሃፉ 4 ነጥብ 18 በ3 ነጥብ 77 ሜትር ሲለካ፥ 1 ሺህ 420 ኪሎ ግራም ክብደት እንዳለው ተገልጿል።

በአባትና ልጅ የተዘጋጀው መጽሃፍ 360 ገጾች አሉት።

አባትና ልጁ ቤላ እና ጋቦ ቫርጋ የተጠቀሙት ባህላዊ መንገድና አዘገጃጀት መጽሃፉን ከመጠኑ ባለፈ ልዩ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

ምንጭ፡- ኦዲቲ ሴንትራል

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.