Fana: At a Speed of Life!

ከመተከል የጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ሁለት ተጨማሪ ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከመተከል የጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ሁለት ተጨማሪ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ ÷ዛሬ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ አንዱ ናቸው፡፡
ሌላው የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ምስጋና እንጂፈታ በመተከል የጸጥታ ችግር እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠራቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

የዞኑ ሠላም ወደ ቀደመ ሁኔታ እስኪመለስ ከጸጥታ ችግሩ ጋር እጃቸው ያላባቸውን አመራሮች ጨምሮ ሌሎችንም ግለሰቦች የማደን ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አቶ ሙሳ ጨምረው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ቀደም ሲልም በተመሳሳይ ችግር የተጠረጠሩ ስድስት ከፍተኛ አመራሮችና አንድ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን በወቅቱ ተገልጿል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.