Fana: At a Speed of Life!

ከምንጊዜውም በላይ በአሁኑ ወቅት ኀብረታችን ግዴታ ነው – ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከምንጊዜውም በላይ በአሁኑ ጊዜ የአፍሪካውያን ኀብረት ግዴታችን ነው አሉ።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የአፍረካ ቀንን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በተቃወሰው ዓለም አቀፍ ሥርዓት የተነሳ አፍሪካ ውስብስብ ፈተናዎች ተደቅነውባታል ብለዋል፡፡

ተቋሞቻችንና ያሉን ማስፈጸሚያ ስልቶች ክፉኛ ተፈትነዋል በማለት የገለጹት ፕሬዚዳንቷ ፥ ከምንጊዜውም በላይ ሕብረታችን ግዴታ ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አክለውም ልጆቿ ለዚህ የጋራ ዓላማ ብቁ ሆነን መገኘት ይጠበቅብናልም ነው ያሉት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፡፡

እኢአ በ1963 የተቋቋመው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምሥረታ የሚታሰብበት “አፍሪካ ቀን” በትናትናው ዕለት ተከብሮ መዋሉ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.