Fana: At a Speed of Life!

ከሮያል ሳንድረስት የጦር አካዳሚ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነው የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው ለገሰ ሞገስ በወታደራዊ መኮንንነት በዓለም ዝነኛ በሆነው የሮያል ሳንድረስት የጦር አካዳሚ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።
 
የሮያል ሳንድረስት የጦር አካዳሚ ከተለያዩ ሀገሮች የመከላከያ ተቋማት ለከፍተኛ ወታደራዊ መኮንንነት እየተቀበለ የሚያሰለጥን ዕውቅ ተቋም ነው፡፡
 
ባለፈው ዓመት ከ38 ሀገሮች ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችን መልምሎ በሰጠው ወታደራዊ ስልጠና ኢትዮጵያዊው ለገሰ ሞገስ ከሁሉም ሀገሮች ሰልጣኞች በሁሉም ወታደራዊ የጥበብ መስኮች በጦር መኮንንነት በጦር ንድፈ ሀሳብ እና በጦር ተግባራዊ ሳይንስ መስክ ባሳየው ጥበብና እውቀት የላቀ ብልጫ በማግኘቱ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
 
ለገሰ ሞገስ ዘመኑ የደረሰበትን ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ በተሟላ መልኩ በመፈጸሙ የጦር አካዳሚው የሚሰጠውን ከፍተኛ ሜዳሊያ፥ከመላው ሀገሮች የተወከሉ ወታደራዊ የጦር መኮንኖች፣ የእንግሊዝ ልዑላዊ ቤተሰቦች፥ የተለያዩ ሀገሮች አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች እንዲሁም የሮያል ሳንድረስት የጦር አካዳሚ አመራሮች በተገኙበት ከእንግሊዝ ልዕልት አን እጅ ነው የወርቅ ሜዳሊያውን የተቀበለው።
 
በምረቃው ስነ-ስርአት ላይ የተገኙት በለንደን የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ እንደተናገሩት ÷ይህ ወጣት የጦር መኮንን ዘመኑ ያፈራውን ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ በብቃት አጠናቆ የላቀ ውጤት በማምጣቱ እና የሀገሩን ስም በምረቃው ስነ ስርአት ላይ በክብር እንዲነሳ ማድረጉ ለሁሉም ኩራት ነው ብለዋል።
 
ኢትዮጵያዊያን በየተሰማራንበት በትጋት ከሰራን ለማሸነፍ ምንም የሚያግደን ምክንያት እንደሌለ የዛሬው የክብር ተመራቂ ለገሰ ሞገስ አርአያ በመሆን ያስመሰከረ ነውም ብለዋል፡፡
 
ከበርካታ ዓመታት በኋላ በሮያል ሳንድረስት የጦር አካዳሚ የወታደራዊ መኮንንነት ትምህርት እድል ያገኘው ለገሰ ሞገስ በበኩሉ÷ ወገኖቼ የሀገራቸውን አንድነት ለማስከበር በዱር በገደሉ እየተዋደቁ እና ህይወታቸውን ለሀገራቸው ክብር እየሰጡ ባሉበት ወቅት ልቤ እነርሱ ጋር ሆኖ ለዚህ ክብር በመብቃቴ ሽልማቱ የእነርሱም ጭምር ነው ብሏል ፡፡
 
የጦር አካዳሚው የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነው ይህ ወጣት መኮንን፥ ለሀገሬ ክብር እና አንድነት ያገኘሁትን አውቀት እና ልምድ በህወይት ጭምር ዋጋ በመክፈል ለማረጋገጥ ዝግጁ ነኝ ማለቱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላከታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.