Fana: At a Speed of Life!

ከሳዑዲ ዓረቢያ 1ሺህ 148 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ ችግር ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 148 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡
 
ከተመላሾቹ ውስጥ 12ቱ ህጻናት ሲሆኑ ÷1ሺህ 136 የሚሆኑትደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
 
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉንም ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ16 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.