Fana: At a Speed of Life!

ከሸኔ እስከ ህወሓት የተኩስ ሩምታ በህይወት የተረፈች ነፍስ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣት ሀብታም ደርበው ትባላለች፤ የወልዲያ ከተማ ነዋሪ ነች፡፡
ወጣት ሀብታም የ16 አመትና የ7ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን፥ በኦሮሚያ ክልል ከቤተሰቦቿ ጋር ትኖርበት ከነበረው አካባቢ አሸባሪው ሸኔ ባደረሰባቸው ግፍ አባቷ ‹‹ለዘር እንኳን ብትተርፊልኝ›› ብለው ወደ ሰሜን ወሎ ወልዲያ አያቶቿ ጋር ያመጧታል፡፡
ለፈተና የተፈጠረች እስኪመስል ድረስ በወልዲያ ደግሞ ከሌላኛው የሽብር ቡድን ህወሓት ጋር አስገድደው ለመድፈር ባደረሱባ ሙከራ ትንቅንቅ ውስጥ ገብታ በእግሯ እና ጭንቅላቷ ላይ ከወረደባት የተኩስ እሩምታ በተዓምር ከሞት መትረፏን ሀብታም ደርበው ገልጻለች፡፡
ሀብታም እንደተናገረችው፥ ላለመደፈር ተናንቃ ስታመልጥ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባት የግራ እግሯ ተመትቷል፤ ይህም አልበቃ ብሏቸው ጭንቅላቷን መትተው የመግደል ሙከራ አድርሰውባታል።
ሃብታም ከሞት ብታመልጥም ጭኗ ላይ በደረሰባት የጥይት ድብደባ አካል ጉዳተኛ ሆናለች።
“አሸባሪው ህወሓት አባላት ወልዲያ ከተማን በተቆጣጠሩበት ወቅት በአንድ ምሽት ወደ ቤት በመምጣት አራት ጓደኞቼን ደፍረዋቸዋል።
በዛች ምሽት አልደፈርም በማለቴና በመሸሼ የተኩስ እሩምታ ከፍተው የግራ እግር ታፋዬን መትተው የአካል ጉዳት አድርሰውብኛል፤ ለመግደልም ወደ ጭንቅላቴ ተኩሰዋል” ብላለች።
እርሷን ለመድፈር ሙከራ ሲያደርጉ በጥይት እሩምታ መሐል ጭንቅላቷና እግሯ ቆስሎም ቢሆን ከመደፈር ማምለጧን ለኢፕድ ገልጻለች፡፡
ሀብታም ከመደፈር ስታመልጣቸው የተኩስ እሩምታ አወረዱባት፤ በእግሯ እና ጭንቅላቷ ላይ ተመትታ ስትወድቅም ሞታለች ብለው ጥለዋት እንደሄዱ ባለታሪኳ ተናግራለች፡፡
አልተሳካላቸውም እንጂ ሌላም ሰው ለመግደል ሞክረው ነበር ስትል ሁኔታውን ታስታውሳለች።
ለዘር የተረፈች ነፍስ፤ ከሁለት የሽብር ቡድኖች በተዓምር ተርፋለች።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.