Fana: At a Speed of Life!

ከባድ የወፍ ጉንፋን በእስያ እና አውሮፓ መከሰቱ ተሰማ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከባድ የወፍ ጉንፋን በእስያ እና አውሮፓ መስፋፋቱን ለዓለም አቀፉ የእንስሳት ጤና ተቋም የደረሰ ሪፖርት አመላከተ።
ኤች 5 ኤን 6 የተባለው ቫይረስ በእስያ ደቡብ ኮሪያ፣ ቻይና እና ጃፓን በከፍተኛ ደረጃ መዛመቱም ነው የተገለጸው።
በደቡብ ኮሪያ በሚገኝ የዶሮ እርባታ ጣቢያ ቫይረሱ በ770 ሺህ ዶሮዎች ላይ መከሰቱን ተከትሎ ዶሮዎቹ መታረዳቸውንም ሪፖርቱ አመላክቷል።
በቻይና በዚህ አመት ቫይረሱ በ21 ሰዎች ላይ የተገኘ ሲሆን ይህም ባለፈው አመት በአገሪቱ ከተመዘገበው የቫይረሱ ስርጭት ከፍ ያለ መሆኑን ቲ አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።
ከዚህ ባለፈም በተያዘው የፈረንጆቹ አመት ፀደይ ወቅት ላይ ይሄው ቫይረስ በሰሜን ምስራቅ ጃፓን በሚገኝ ዶሮ እርባታ ጣቢያ ላይ መከሰቱም ተሰምቷል።
በተመሳሳይ ቫይረሱ በአውሮፓ ቤልጂየም፣ ኖርዌይ፣ ፈረንሳይ እና ኔዘርላንድስ በዶሮ እርባታ ጣቢያዎች ተከስቷል ነው የተባለው።
የቫይረሱን መዛመት ተከትሎም በሚሊየን የሚቆጠሩ አዕዋፍ እና ዶሮዎች እንዲወገዱ ምክንያት ሆኗል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.