Fana: At a Speed of Life!

ከተለያዩ ሚኒስቴር መ/ቤቶች የተውጣጣ ቡድን የልማት ሥራዎችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር፣ የተለያዩ ሚኒስቴር መ/ቤቶች እና የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ተወካዮችን ያካተተ ቡድን ኢትዮጵያ እያካሄደችው ከምትገኘው የኅብረ ብሄራዊ ዘመቻ ጎን ለጎን የሚካሄዱ የልማት ሥራዎችን ጎበኘ፡፡
ጉብኝቱ በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የክትትልና ግምገማ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ጥሩማር አባተ የተመራ ሲሆን÷ ኅዳር 27 የተጀመረው የልማት ሥራዎች ጉብኝት እስከ ታህሳስ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡
ልዑኩ ባካሄደው ጉብኝት÷በወራቤ ከተማ የሚገኘውን ካሌድ ጂጆ እንዲሁም በአዳማ ከተማ የሚገኘውን 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ፣ የመልካሳ-ሶደሬ-ኑራሄራ-መተሀራ ፕሮጀክቶችን ተመልክቷል፡፡
በጉብኝቱም ከልማት ፕሮጀክቱ ተቋራጮችና አማካሪ ድርጅቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ፕሮጀክቱ ከተገነባበት አካባቢ ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ተወያይቷል፡፡
በቀጣይ የኢተያ-ሮቢ አገናኝ መንገድ ልማት ፕሮጀክት በሚገነባበት አካባቢ እና አሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በማቅናት ከተቋራጮች፣ አማካሪ ደርጅቶች እና ከአካባቢው የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እንደሚወያይ ይጠበቃል፡፡

መርሃ ግብሩ በአዲስ አበባ አደይ አበባ ስታዲየምን በመጎብኘት የሚጠናቅቅ ይሆናል መባሉን ከፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.