Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ በአፋር ክልል ጉዳት የደረሰባቸውን ጤና ተቋማት ስራ ለማስጀመር የሚረዳ የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት የደረሰባቸውን ጤና ተቋማት ስራ ለማስጀመር የሚረዳ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አስረከበ፡፡
ተደረገው ድጋፍ÷ የተለያዩ የህክምና መድሃኒቶች፣ የህክምና መሳሪያዎች እና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያ ግብአቶች ያካተተ ነው መባሉን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያትያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ድጋፉን የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ያስረከቡ ሲሆን÷ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ እና የአፋር ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ ያሲን ሀቢብን ጨምሮ ሌሎች ተወካዮችም ተገኝተዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.