Fana: At a Speed of Life!

ከተሞች በሁለተናዊ መስኮች ድርሻቸውንና እድገታቸውን ለማፋጠን በእቅድ የተመሩ ሊሆኑ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ከዩ ኤን ሀቢታት ጋር በመተባበር በክልላዊ ስፓሻል ልማት ዝግጅት የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ተጀምሯል።
በመድረኩ ላይ የፌደራል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ የክልሎች የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የፌደራል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የከተሞችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገታቸውን በማፋጠን የልማት ማዕከል እንዲሆኑ ለማስቻል በከተሞች በእቅድ የተመራ የአሰራር ስርአትን መዘርጋት ያስፈልጋል ብለዋል።
የክልሎች የእስፓሻል የልማት እቅድ ከተሞች ሚናቸውንና የልማት ማዕከልነታቸውን የሚያሳድግ ፍኖተ ካርታ መሆኑን ጠቁመው በውይይቱ የተሳተፉ የዘርፉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በእቅዱ ዝግጅት ላይ በጥልቀት በመወያየት ለእቅዱ ስኬታማነት በቁርጠኝነት እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ አቅርበዋል።
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ እስፓሻል የልማት እቅዱ ከተሞች በሁለንተናዊ መስኮች ያላቸውን ድርሻና እድገታቸውን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ ከለውጡ በፊት ከተሞች ተረስተው መቆየታቸውን የገለፁት ርዕስ መስተዳድሩ በአሁኑ ጊዜ የከተሞችን ልማትና እድገት የሚያረጋግጡ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው የክልሉ መንግስት ለእስፓሻል የልማት እቅዱ ተግባራዊነት የሚጠበቅበትን አስተዋፆ እንደሚያበረክት ጠቅሰዋል።
የውይይት መድረኩ ላይ የክልሎች የእስፓሻል እቅድ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን የውይይት መድረኩ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.