Fana: At a Speed of Life!

ከተሳሳተ የአወቃቀር ለዉጥ ጋር ተያይዞ ተቋርጦ የነበረዉ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ተመልሷል-የፌስቡክ ካምፓኒ

አዲስ አበባ፣መስከረም 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌስቡክ ፣ ዋትሳፕ እና ኢንስታግራም ትናንት  ለስድስት ሰዓታት ያህል  ከተቋረጡ በኋላ ተመልሰዋል ሲል የፌስቡክ ካምፓኒ አስታወቀ፡፡

ተቋርጦ የነበረዉ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ከተሳሳተ የአወቃቀር ለዉጥ ጋር ተያይዞ   መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የፌስቡክ ካምፓኒዉ በመግለጫዉ÷ የማህበራዊ ሚዲያው ተቋርጦ በነበረበት ወቅት የተጠቃሚ ግላዊ መረጃ ተጥሷል የሚል ማስረጃ የለም ብሏል፡፡

የአገልግሎት መቋረጥን የሚከታተለው ዳውደክተር÷እስካሁን በዓለም ዙሪያ 10 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚሆኑ የችግር ሪፖርቶች እንዳሉ ተናግረዋል።

የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ በመቋረጡ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ይቅርታ ጠይቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.