Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባዎች በየከተሞቻቸው ያሉ ጸጋዎችን በመለየት ለስራ እድል ፈጠራ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)“የተሻለ ከተማ ለተሻለ ህይወት” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ተጠናቀቀ፡፡
ፎረሙ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ፣ የፌደራል እና የክልል የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የከተሞች ከንቲባዎች በተገኙበት ነው የተጠናቀቀው።
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ የኢትዮጵያ ከንቲባዎች ፎረም የቦርድ ሰብሳሲ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንዳሉት÷ በከተሞች የመልካም አስተዳደርን ማስፈን፣የስራ እድል ማስፋት ፣የመኖሪያ ቤት እና የመሠረተ ልማት አቅርቦትን ማሻሻል ይገባል።
የሁሉም ከተሞች ከንቲባዎች በየከተሞቻቸው ያሉ ጸጋዎችን በመለየት ለነዋሪዎቻቸው ውብ እና ምቹ አካባቢን ከመፍጠር ባለፈ ለስራ እድል ማመቻቸት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባም አውስተዋል።
የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ከንቲዎባች ፎረም ዋና አላማ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከንቲባዎች በቋሚነት ተገናኝተው ስለከተሞች ጉዳይ የሚመካከሩበት መሆኑን አንስተዋል፡፡
እንዲሁም የዕርስ በርስ ትስስር የሚፈጥሩበት፤ በችግሮች ዙሪያ በጋራ መፍትሄ የሚፈልጉበት መድረክ ለማመቻቸት በማሠብ የተቋቋመ መሆኑን ገልፀው ሁሉም የከተሞች ከንቲባዎች በሃላፊነትና በትብብር መንፈስ ሊሠሩ ይገባል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.