Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ከ6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነቡ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ከ6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነቡ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡

ከንቲባዋ በዚህ ወቅት ፥ ፕሮጀክቶቹ በታሰበላቸው ጊዜ በፍጥነት እንዲሁም ጥራታቸውን ጠብቀው ስለሚጠናቀቁበት ሁኔታ ከየፕሮጀክቶቹ የስራ ተቋራጮችና አማካሪዎች ጋር ተነጋግረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተዘዋውረው ከተመለከቷቸው ፕሮጀክቶች መካከል የአፍሪካ ኢኖቬሽን ማእከል፣ የአዲስ አበባ ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ፣ የታላቁ የቅርስና የመኪና ማቆሚያ ፕሮጀክትና የካ ቁጥር ሁለት መኪና ማቆሚያ ይገኙበታል፡፡

ፕሮጀክቶቹ የገጠማቸውን የሲሚንቶና የውጪ ምንዛሬ እጥረት በመቅረፍ ጥራታቸውን ጠብቀው በብቃት የመጨረስ አቅም ማሳደግ እንደሚገባም ከንቲባዋ መናገራቸውን ከከተማው ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.