Fana: At a Speed of Life!

የሰዓት እላፊ ገደቡ አምራች ኢንዱስትሪዎችን እንደማይመለከት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ባስተላለፈው መመሪያ በአንዳንድ አካባቢዎች የተቀመጠው የሰዓት እላፊ ገደብ ሁሉንም አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደማይመለከት አስታውቋል።
አምራች ኢንዱስትሪዎቹ አስፈላጊ የሆነ የራሳቸውን የጥበቃ ስርዓት ከወትሮው በተለየ መልኩ አጠናክረው መደበኛ ስራቸውን በተለመደው ሁኔታ እንዲቀጥሉ ነው ዕዙ ያስታወቀው።
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ የተላለፈው መመሪያ የሚከተለው ነው፦
አሁን ባለው ሀገር የማዳን ግዳጅ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወቃል፡፡
በዚህ ምክንያትም በአንዳንድ አካባቢዎች የሰዓት እላፊ ገደብ የተደረገ ቢሆንም በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ገደቡን ተግባራዊ ማድረግ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ጫና ስለሚያሳድርና ኢንዱስትሪዎችንም ወደ ኪሣራ ስለሚያስገባቸው የተቀመጠው የሰዓት እላፊ ገደብ ለሁሉም አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደማይመለከት ታውቆ፤ ኢንዱስትሪዎቹ አስፈላጊ የሆነ የራሳቸውን የጥበቃ ስርዓት ከወትሮው በተለየ መልኩ አጠናክረው መደበኛ ስራቸውን በተለመደው ሁኔታ እንዲቀጥሉ እንዲደረግ ነው ያሳሰበው፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.