Fana: At a Speed of Life!

ከአሸባሪው ህውሓት ጋር በምናደርገው ውጊያ የህዝባችን ድጋፍ አቅም ሆኖናል- በግንባር የተሰለፉ የጸጥታ ኃይሎች

አዲ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውን ቡድን በግንባር ስንዋጋ ማህበረሰቡ ደጀን በመሆን የሚሳየው አለኝታነት የሚበረታታ መሆኑን በወሎ ግንባር የተሠለፉ የጸጥታ ሀይሎች ገለጹ፡፡
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የጋዜጠኞች ቡድን በወሎ ግንባር ቅኝት ባደረገበት ወቅት የጸጥታ ኃይሎች እንደገለጹት÷ ወራሪውና ዘራፊውን ቡድን ባለበት ለመቅበር እየሠራን ነው ብለዋል።
ረዳት ኢንስፔክተር መስፍን መኮንን እንደተናገሩት÷ እኛ መስዋእትነት ስንከፍል ማህበረሰቡ እያሳየ ያለው ደጀንነት ስንቅና ሞራል ሆኖናል ብለዋል።
ምክትል ሳጅን ሰለሞን ሙጨ በበኩላቸው÷ ጁንታው በግንባር ስንፋለም ማህበረሰቡ ከኘሮፖጋንዳ በመራቅ አካባቢውን ነቅቶ ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል።
ከሀሠት ወሬ በመራቅ አካባቢውን በንቃት መጠበቅ አለበት ያሉት የጸጥታ ሀይሎቹ÷ ወጣቱ ግንባር ድረስ በመዝመት ሀገሩን ሊጠብቅ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.