Fana: At a Speed of Life!

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተላለፈ መልዕክት:-

የተከበራችሁ ውድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ፤ የጥምቀት በዓል በሀገራችን ብሎም በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ከሚክበሩ በዓላት መካከል በናፍቆት የሚጠበቅ ነው::

በዓሉ በሀገራችን የኦርቶዶክስ ተውዋህዶ ቤተክርስትያን ለዓለም ያበረከተችው ድንቅ ቅርስ ሲሆን ለእኛ ለኢትዮጵያዋን ደግሞ የኩራታችን ምንጭ ጭምር ነው::

በዘንድሮ የከተራ ፣ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በአላት ላይ የሀገራቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ትውልደ ኢትዩጵያውን ፣ ዲያስፖራዎች እና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲሁም በርከታ ቁጥር ያለው የእምነቱ ተከታዮች ታድመውበታል፡፡

የጥምቀት በዓል የበዓሉን ትውፍታዊ ገፅታውን ጠብቆ በሰላምና በፍቅር: በድምቀትና በአብሮነት መንፈስ በማክበር በአዲስ አበባ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች 266 ታቦታት ከመንበራቸው በመዉጣት በ72 ልዩ ልዩ የጥምቀተ ባህር ስፈራዎች አድረው በሰላም ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡

በዓላት በመጡ ቁጥር ድብቅ ፍላጎታቸውን ለማሳካት የሚፈልጉ ሃይሎች በኢትዮጵያ ሰላም የለም ለማስባልና የአሸባሪውን ቡድን ተቀጥላ ፍላጎቶች ለማስፈፀም፤ በህዝብ የተመረጠን መንግስት በአመፅና ግርግር ለማውረድ ፤ በህዝቦች መሃከል ጥርጣሬና ግጭት ለመፍጠር፤ ብሎም ህዝባዊ በአሉን ወደለየለት ትርምስ ለመክተት፤ ህዝብን የሚሸብሩ ድርጊቶችን ለመፈፀም አቅደው ቢንቀሳቀሱም ሀገሩን እምነቱንና ባህሉን አክባሪ የሆነው ህዝባችን ባደረገው ርብርብ በዓሉ ጠላት በተመኘው ልክ ሳይሆን በሰላም ተጀምሮ በሰላም ተጠናቋል::

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአራዳ ክ/ከተማ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ ፀብ አጫሪና አሳፋሪ ድርጊት እንዲሁም ከባህረ ጥምቀቱ ወደ ደብሯ በመመለስ ላይ በነበረችው በወይ ብላ ማርያም ታቦት በቡራዩ ከተማ አዋስኝ አካባቢ የገጠማት መስተጓጎል እና ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው አለመግባባት ህይወታቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የከተማ አስተዳደሩ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶታል፡፡

በዚህ ረገድ እንደ መንግስት የመንግስት አካላት ጥፋት የሆነውን ለይተን እርምጃ መውሰድ የጀመርን ሲሆን በቀረውም አጥፊዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ ሃላፊነታችንን የምንወጣ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡

ከተማችን እንደወትሮዋ ሁሉ በከተማዋ ውስጥ የሚካሄዱ ሃይማኖታዊ ባህላዊ የተለያዩ ክብረ በዓላትና ኩነቶች በድምቀት በሰላም በአብሮነት መንፈስ እንዲካሄዱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እጅና ጏንት ሆኖ መስራቱን ይቀጥላል:;

በከተማችን የጥምቀት በዓል በድምቀትና በስላም እንዲከበር ምዕመኑ መላው የከተማችን ነዋሪወችና የጸጥታ ሃይሎች ላደረጋችሁት ጥረት ለከፈላችሁት ዋጋና ላስያችሁት ጨዋነት የከተማ አስተዳደሩ የላቀ ምስጋነውን ያቀርባል:: ይህንኑ በቅርቡ በሚጠበቀው በእፍሪካ መሪወች ጉባኤ በሰላም ውብና ጽዱ በሆነ አካባቢ እና በማራኪ አቀባበልና አገልግሎት የበለጠ እንዲትዘጋጁ አደራ እንላለን::

በመጨረሻም ህዝብ እያደረገ ላለው ጠንካራ ድጋፍ እና በአላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ ሁሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን!!

የከተማችንን ሰላም በማረጋገጥ የጀመርነውን የኢትዮጵን ትንሳኤ የማረጋገጥ ተግባር አጠናክረን እንቀጥላለን!!
ጥር 14/2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.