Fana: At a Speed of Life!

ከአጋር አካላት ጋር ለኢትዮጵያ ድጋፍ ለማድረግ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የአውሮፓ ሕብረት ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በመተባበርና በመነጋገር በተለያየ መንገድ ኢትዮጵያን ለማገዝ እየሠራ መሆኑን የአውሮፓ ሕብረት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የአውሮፓ ሕብረት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ዣኔዝ ሌናርቺቺ እና የ13 አገራት የአውሮፓ ሕብረት ቡድን አባላት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ኮሚሽነር ዣኔዝ ሌናርቺቺ በጉብኝታቸው ወቅት÷ የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡
ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በመተባበርና በመነጋገርም በተለያየ መንገድ ኢትዮጵያ ለማገዝ እየሠራ እንደሆነ ገልፀዋል።
ኮሚሽነሩ እና የሕብረቱ አባላት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታልን ከጎበኙ በኋላ÷ ለሆስፒታሉ የሚያስፈልጉ የድጋፍ አይነቶችን መለየታቸው ተመላክቷል።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያን በበኩላቸው÷ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድና ሪፈራል ሆስፒታል ባደረጉት ጉብኝት በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች እንደተመለከቱ ተናግረዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አሸናፊ ታዘበው እንደገለጹት÷ ሆስፒታሉ በዚህ ዓመት ብቻ በጦርነት ጉዳት ከደረሰባቸው ወገኖች ውጪ ከ400 ሺህ በላይ ተመላላሽና ከ35 ሺህ በላይ ተኝተው የሚታከሙ ህሙማንን አስተናግዷል፡፡

የአውሮፓ ሕብረት ልዑክ ሆስፒታሉ እየሰጠ ያለውን አገልግሎትና ያለበትን ችግር እንደተመለከተ እና በቀጣይ አስፈላጊ ድጋፎች በሚደረግባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡

በሙሉጌታ ደሴ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.