Fana: At a Speed of Life!

ከአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር እየተወያየች ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ከ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ውይይት እያደረገች ነው።

እስካሁን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር በሚያስችሉና በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ከቤኒን፣ ከአልጄሪያ፣ ከላይቤሪያ፣ ከቡሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ውይይቶች ተደርጓል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተለያዩ ሃገራት አቻዎቻቸው ጋር ውይይቶችን ያደረጉ ሲሆን÷ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ ነጥቦች መነሳታቸውን የውጭ ጉዳይ ቃለአቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.