Fana: At a Speed of Life!

ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ጠንካራ ግንኙነት ይኖረናል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)) “ከአዲሱ የኢትዮጵያ መንግስት ጋር ጠንካራ ግንኙነት ይኖረናል” ሲሉ የተለያዩ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎች ገለጹ።
የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ሃላፊዎች፤ የመንግስት መስረታ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ለሚኖራት ግንኙነት አዲስ ምእራፍ የሚከፍት መሆኑን ገልጸዋል።
የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃመድ አሊ የሱፍ፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አንድነት በቁርጠኝነት የሰራች አገር ናት ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያ አሁን ላይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለፈች መሆኑን ጠቅሰው ሆኖም “ኢትዮጵያውያን ችግራቸውን በራሳቸው አቅም መፍታት የሚችሉ ጠንካራ ህዝቦች መሆናቸውን ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል” ብለዋል።
ጀቡቲ ሁሌም ከኢትዮጵያውያን ጎን የምትቆም ጠንካራ አቋም ያላት አገር መሆኗንም ነው ያብራሩት።
ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ወዳጅነት ከሌሎች ሀገራት ጋር ካላት ግንኙነት ይለያል የሚሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ÷ ሁለቱ ሀገሮች በመሰረተ ልማት ጭምር የተሳሰረ ጥብቅ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የተመሰረተው አዲስ መንግስት የሁለቱ አገራት ግንኙነትን ወደ አዲስ አድማስ እንደሚያሸጋግረው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ ጆን ሙሊምባ÷ ኡጋንዳና ኢትዮጵያ በምንም አይነት ሁኔታ የማይቀየር አጋርነት እንዳላቸው ጠቁመዋል።
ሁለቱ አገሮች የአፍሪካ ቀንድን ወደ አንድ ለማምጣትና በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን በጋራ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም ይህንኑ ተግባር አጠናክረው አንደሚቀጥሉ አውስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ኢትዮጵያን ለመምራት ድጋሚ እድል ስለተሰጣቸው መደሰታቸውንም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ በሆነ አዲስ መንግስት መመስረታቸው የሚደነቅ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ናቸው።
እስራኤል በዴሞክራሲ በጽኑ የምታምን ሀገር መሆኗን ጠቅሰው÷ ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲያ ሂደት መንግስት መቋቋሟ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በጎ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.