Fana: At a Speed of Life!

ከ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ መድረክ በኃላ 34 የተዘጉ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ ተመልሰዋል- የሲዳማ ከልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ መድረክ በኃላ 34 የተዘጉ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ መመለሳቸውን የሲዳማ ከልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የሲዳማ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ “ ኢትዮጵያ ታምርት” የሚለው ንቅናቄ በክልል ደረጃ ከተጀመረ በኃላ 34 ሥራ ያቆሙ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ መመለሳቸው ገልጸው÷ ሌሎች ኢንዱስትሪዎችም በተሻለ ሁኔታ ምርታቸውን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ እያስገኙ ነው ብለዋል ፡፡
ከኤሌክትሪክ እና የካፒታል እጥረት እንዲሁም የክህሎት ችግርና የመሠረተ ልማት አቅርቦቶች ደረጃ በደረጃ እየተፈተኑ በመሆኑ ከ “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ወዲህ ብዙ ኢንዱስትሪዎች ወዳ ሥራ መግባታቸውን የሲዳማ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.