Fana: At a Speed of Life!

“ከኢድ እስከ ኢድ መርሐ ግብር ኢትዮጵያን በብዙ መልኩ ለዓለም የምናስተዋውቅበት መድረክ ነው” – አምባሳደር ብርቱካን አያኖ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢድ እስከ ኢድ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ያላትን ሃይማኖታዊ ታሪካዊና ማህበራዊ ሀብቶች በሚገባ ለዓለም የምታስተዋውቅበት መልካም አጋጣሚ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተናገሩ።
ሚኒስትር ዴኤታዋ ይህንን ያሉት “ከኢድ እስከ ኢድ” መርሐ ግብር አንድ አካል የሆነው ኢድ-ኤክስፖ” ዛሬ በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት ነው።
ከኢድ እስከ ኢድ መርሐ ግብር “የታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት” ቀጣይ ምዕራፍ መሆኑን አስታውሰው÷ ዳያስፖራዎች ሀገራቸውን በብዙ መልኩ እንዲያግዙ ያለመ ሀገራዊ ጥሪ መሆኑን አንስተዋል።
ዛሬ በይፋ የተከፈተው ኤክስፖም የላቀ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው በመሆኑ÷ ዳያስፖራዎች እየጎበኙና እየሸመቱ የኢትዮጵያን ምርት እንዲያስተዋውቁ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ ኢንድሪስ በበኩላቸው÷ ዳያስፖራው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጥሪ በመቀበል ወደ ሀገሩ ለመምጣት እያሳየ ያለው ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ ቀናትም በአዲስ አበባ እና በክልሎች በሚኖሩ መርሐ ግብሮች ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የሀገርና የወገን አለኝታነቱን በተግባር እንዲገልፅ ጥሪ መቅረቡን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ÷ ዳያስፖራው በሀገር ቆይታው በወጡ መርሐ ግብሮች ላይ ሁሉ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ሀገሩንና ወገኑን የማገዝ ስራ ላይ በመሳትፍ ወገናዊ አደራውን መወጣት አለበት ብለዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.