Fana: At a Speed of Life!

ከከተማ አቀፉ ኤግዚቢሽንና ባዛር 27 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ኅበረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ ባለፉት ቀናት ባካሄደው ከተማ አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር 27 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለፀ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ዓሊ እንደገለፁት÷ በተዘጋጀው ኤግዚቢሽን፣ በዛርና ሲምፖዚየም የኅብረት ሥራ ማኅበራትና የተለያዩ ተቋማት ተሳትፈዋል፡፡
በበዛሩም÷ከአዲስ አበባና ከስድስት ክልሎች በተለያዩ የኅብረት ሥራ ዘርፎችና ከኅብረት ሥራ ሴክትር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ተቋማት ተሳትፈዋል ብለዋል፡፡
በዚህም የተለያዩ ምርቶችን በማስተዋወቅ የግብርና የኢንዱስትሪ ምርቶችና የዕደ ጥበብ ውጤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሽያጭ ማቅረባቸውንም ነው የገለጹት፡፡
በዚህም በከተማዋን የገበያ ዋጋ ማረጋጋት ተችሏ መባሉን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኤጀንሲውም እንደ ኅብረት ሥራ ማኅበርም ካዘጋጀው ከተማ አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር 27 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.