Fana: At a Speed of Life!

ከካሊፎርኒያ፣ ጀርመንና ቱርክ የመጡ ዳያስፖራዎች ለተፈናቃዮች ከ14 ሚሊየን በላይ ድጋፍ  አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ) አገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ከአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት፣ ከጀርመንና ቱርክ የመጡ ዳያስፖራዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል ከ14 ነጥብ 3 ሚለየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በካሊፎርኒያ ሳክራሜንቶ ከተማ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተወካይ አቶ አደም ለገሰ የተሰባሰበውን 247 ሺህ 670 ዶላር  ለብሔራዊ አደጋ ሥጋት አመራር ምክትል ኮሚሽነር አይድሩስ ሃሰን  አስረክበዋል።

የገንዘብ ድጋፉን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክትም፥ ኢትዮጵያ ተገዳ በገባችበት ጦርነት በዜጎች ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን አንስተዋል።

አቶ ትርፌ ፍቃዱ ደግሞ ከጀርመን ባቫሪያ ስቴት የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ያሰባሰቡትን ከ1 ሚሊየን 34 ሺህ ብር በላይ ለኮሚሽኑ አስረክበዋል።

በተመሳሳይ በቱርክ የሚኖሩና የታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ጥሪን ተቀብለው የመጡ ዳያስፖራዎች አንድነትና ትብብር ማህበር አባላት ለተፈናቀሉ ወገኖች ያሰባሰቡትን 27 ሺህ ዶላር አስረክበዋል።

የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት አመራር ምክትል ኮሚሽነር አይድሩስ ሃሰን በበኩላቸው÷ ዳያስፖራዎቹ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

ዳያስፖራዎቹ በቀጣይም የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.