Fana: At a Speed of Life!

ከኮሮና ቫይረስ ለመጠበቅ ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት መነሻውን ቻይና ያደረገውን የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን አውጇል።

ከዚህ ባለፈ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዓለም ህዝብ ላይ ከፍተኛ ስጋትን በደቀነው እና በርካቶች ለህልፈተ ህይወት ከዳረገው ቫይረስ ራስን መጠበቅ እንደሚገባ ነው የተነገረው።

ጥንቃቄዎቹም፡-

1. በሕይዎት ካሉም ሆነ ከሞቱ የቤትና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ

2.ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ

3. የትኩሳትና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣

4. እጅን በሳሙናና ውሃ መታጠብ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ከፈጠሩ፣

እንዲሁም በበሽታው መያዛቸውን የጠረጠሩ ሰዎች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች ደግሞ÷

ወደ ሀገር በተመለሱ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ የመተንፈሻ አካል ህመም፣ ትኩሳትና እንደሳል ያሉ የህመም ምልክቶች ካለብዎት ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት ማግኘት፣

የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አስራ አራት (14) ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገራት ሄደው ከነበረ ይህንንም ለጤና ባለሙያው ማስረዳት፤

በሚያስሉበትናበሚያስነጥሱበትጊዜበሽታውወደጤነኛሰውእንዳይተላለፍአፍናአፍንጫንበክንድ፣በመሃረብወይምበሶፍትመሽፈን፣

አፍና አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡

በሽታውን ሪፖርት ወደ አደረጉ ሀገራት ሄዶ የበሽታውን ምልከቶች ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቋም ማሳወቅ ወይም ከታች በተገለፁት አድራሻዎች በመጠቀም ሪፖርት ማድርግ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

8335

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.