Fana: At a Speed of Life!

ከኮቪድ ህክምና አገግመው የወጡ ታካሚዎች የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ለሆስፒታሉ ሰራተኞች ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 29 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮቪድ-19 ተይዘው በቡልቡላ ኮቪድ ለይቶ ህክምና መስጫ ፊልድ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና አግኝተውና አገግመው የወጡ ታካሚዎች የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ በሆስፒታሉ አገልግሎት ለሚሰጡ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ምንም እንኳን ህመሙ ከባድ ቢሆንም በሆስፒታሉ የነበራቸው ቆይታ መልካም እንዲሆን ሁሉም ሰራተኞች በመልካም አገልግሎት ተንከባክበው ጤናቸው እንዲመለስ ማስቻላቸውን ታካሚዎቹ ገልጸዋል፡፡
ታካሚዎቹ በሽታው ቢይዛቸውም እንኳን የሚበገሩ የማይመስላቸው የነበረ መሆኑን ገልጸው ሁሉም ሰው ሳይዘናጋ ራሱን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የህክምና ባለሙያዎችም ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው እያገለገሉን በመሆኑ እነሱም ወደ መደበኛ ህይወታቸውና ስራቸው እንዲመለሱ የሚያስተላልፉትን መልዕክቶች ማህበረሰቡ ቸል ሳይል እንዲተገብር ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የፊልድ ሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶክተር ሜላት ሰብስቤ በበኩላቸው÷ ማንኛውም ጤና ባለሙያ የሚያክመው ታካሚ ድኖ ከማየት ውጪ የሚያረካው ምንም ነገር የለም ብለዋል።
ከኮቪድ 19 አገግመው የወጡ ታካሚዎችም የኮቪድን አስፈሪና አስደንጋጭ ገፅታዎችን አይተው ስለተመለሱ ለህብረተሰቡ መነቃቃት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የፊልድ ሆስፒታሉ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ወደ አራት መቶ የሚጠጉ ታካሚዎችን ተቀብሎ ማስተናገዱን ከቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.