Fana: At a Speed of Life!

ከዋጋ መናር ጋር በተያያዘ የተከሰተውን ችግር ለመጋፈጥ መዘጋጀት ያስፈልጋል – አቶ ክቡር ገና

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዋጋ መናር ጋር በተያያዘ የተከሰቱ ችግሮችን ሕብረተሰቡ ለመጋፈጥ መዘጋጀት እንዳለበት የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤት ኃላፊ ክቡር ገና አስታወቁ፡፡

መንግሥትና መላው ሕዝብ በኢኮኖሚው ዘርፍ ከዋጋ መናር ጋር በተያያዘ እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመጋፈጥ በአንድነት መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡

አቶ ክቡር ገና ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት ከዋጋ ንረት ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን ችግር ለመከላከል መንግሥትና ሕዝብ አንድ ላይ ሆነው ችግሩን ለመጋፈጥ መንቀሳቀስ አለባቸው።

መንግሥትም በተቻለ መጠን ቁጥጥሩን ማጥበቅ ይኖርበታል ብለዋል።

አንዳንድ ነጋዴዎች በዚህ የፈተና ወቅት መጠቀም አለብን በሚል ባልተገባ መልኩ ሲንቀሳቀሱ እንደሚታዩ ያመለከቱት አቶ ክቡር፥ በዚህም ለህብረተሰቡ መድረስ ያለበት ምርት በትክክል እንዳይደርስ በማድረግ የሚፈጠር አሻጥር መኖሩን ነው የጠቆሙት።

በተለይ ጦርነት በሚነሳበት ወቅት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ስለሚከሰት በዚህ ወቅት ለመጠቀም የሚፈልግ ነጋዴ እንደሚኖር ይታመናልም ብለዋል።

በኢትዮጵያ የዶላር ምንዛሪ ከፍተኛ እጥረት አለ በሚል ሰበብ እንዲሁም ወደፊት ይወደዳል በሚል እሳቤ ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎች አሉ ያሉት አቶ ክቡር÷ ይህም የዶላር ዋጋ እየጨመረ ስለሚሄድ ሊተካ በሚችል መልኩ ዋጋ መሰብሰብ አለብኝ ከሚል እሳቤ የሚመጣ መሆኑን ገልጸዋል።

እነዚህ ነጋዴዎች በተለይ ከምግብ ጀምሮ እስከ ግንብታ ግብዓት እና ሌሎችም ተፈላጊ ምርቶችን እንደሚደብቁ መናገራቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.