Fana: At a Speed of Life!

ከውጭ የሚገባን የአፈር ማዳበሪያ ጉድለት ለመሙላት የተፈጥሮ ማዳበሪያ ላይ እየተሰራ ነው – የግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከውጭ የሚገባን የአፈር ማዳበሪያ እስከ 20 በመቶ የሚሆነውን ጉድለት መሙላት የሚችል የተፈጥሮ ማዳበሪያ ላይ እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ÷ ኮምፖስትን ጨምሮ የአፈር ለምነትን የሚጨምሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከውጭ የሚገባን ሰው ሰራሽ የአፈር ማዳበሪያ እጥረት እና ክፍተትን ለመሙላት አርሶ አደሩ በቀላሉና በአጭር ጊዜ የሚያዘጋጃቸው የተለያዩ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዓይነቶች ላይ በትኩረት እየሰራን ነው ሲሉም ተናግረዋል።

በክልሎች የተለያየ አፈፃፀም ቢኖርም የተፈጥሮ ማዳበሪያ ላይ በስፋት እየተሰራ እንደሆነም ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

የተፈጥሮ ማዳበሪያ ከውጭ የሚገባን ሰው-ሰራሽ ማዳበሪያ ጉድለት ከመሙላት በተጨማሪ የአፈር ለምነትን በመጨመር የአፈር አሲዳማነትን መከላከል እንደሚችልም የግብርና ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ወደፊት አርሶ አደሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያን በስፋት ማዘጋጀት እና መጠቀም እንደሚገባውም ነው የግብርና ባለሙያዎች ያስረዱት።

በዙፋን ካሳሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.