Fana: At a Speed of Life!

ከደምበል ሃይቅና ከቆቃ ሃይል ማመንጫ ግድብ  እንቦጭን የማስወገድ ዘመቻ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከደምበል ሃይቅና ከቆቃ ሃይል ማመንጫ ግድብ  እንቦጭን የማስወገድ ዘመቻ ዛሬ  በይፋ ተጀመረ፡፡

የዘመቻ ስራውም ከተማ ሃይሌ ሪዞርት አከባቢ በሚገኘው የዝዋይ ሃይቅ ዳርቻ ላይ አባገዳዎችና ተጠሪ እንግዶች እንዲሁም የአከባቢው ህብረተሰብ በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል፡፡

ዘመቻው ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን ÷የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ የተፋሰሶች ልማት ባለ ስልጣን እና ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመሆን ከጣና ሀይቅ አረም የማስወገድ ዘመቻ ስራ የተገኘውን ልምድ በመቀመር ዘመቻውን በማባስተባበር  እንደሚመሩ  ታውቋል፡፡

ዘመቻው  በ980 ሄክታር ላይ በተመረጡ አዋሳኝ ቀበሌዎች ላይ እንደሚሰራም ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ተመሳሳይ ዘመቻ በጣና ሃይቅ ላይ ከጥቅምት 9 እስከ ህዳር 30 ቀን2013 ዓ.ም ድረስ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.