Fana: At a Speed of Life!

ከደሴ እስከ ወልዲያ ያሉት ከተሞች ኤሌክትሪክ ሀይል አግኝተዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደሴ እስከ ወልዲያ ሲከናወን የቆየው ጉዳት የደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ ሀይል መስመሮች የመጠገን ሥራ ትናንት ምሽት ተጠናቆ ከተሞቹ ከ 10:05 ጀምሮ ኃይል ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ።

ጥገናው ትናንት ምሽት ቢጠናቀቅም መስመሩ በሚያልፍበት አካባቢ በደሴ እና በሀይቅ መካከል እንዲሁም መርሳ አካባቢ የበቀለ ዛፍ ከመስመሩ ጋር ተገናኝቶ ባለመቆረጡ የተነሳ ኤሌክትሪክ ማገናኘት አልተቻለም ነበር ብሏል።

ይሁንና ዛሬ ዛፎቹ በመቆረጣቸውና ኃይል ለመስጠት የሚያግድ ነገር ባለመኖሩ ከተሞቹ ኤሌክትሪክ ማግኘት ችለዋል።

ተቋሙ አያይዞም ለወልዲያ ከተማና አካባቢው አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ የተዘረፈው ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያ የሚሰጠውን አገልግሎት የሚተካ ዘላቂ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።

የተጀመረው ሥራ በቀጣዮቹ ከአራት እስከ አምስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ከፍተኛ ኃይል ለመስጠት የሚያስችል ነው ብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.