Fana: At a Speed of Life!

ከግንቦት ወር አጋማሽ ጀምሮ የክረምት ዝናብ በተወሰኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተፅዕኖ እንደሚኖረው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ (ኤፍ ቢ ሲ) ከግንቦት ወር አጋማሽ ጀምሮ የተወሰኑ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የክረምት ዝናብ ተፅዕኖ ውስጥ እንደሚወድቁ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አህመዲን አብዱልከሪም እንደገለጹት፥ ከግንቦት ወር አጋማሽ ጀምሮ የክረምቱ ዝናብ ተፅዕኖ ሊበረታ ስለሚችል በአርሶና አርብቶ አደር አካባቢዎች ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል።

የክረምቱ ዝናብ ተፅዕኖ በኦሮሚያ ክልል ሁሉም የወለጋ ዞኖች፣ ጅማ፣ ኢሉ-አባቦራ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዞኖች፣ በአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብ ጎጃምና የባህር ዳር ዙሪያ፤ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ በሲዳማ ዞኖች ከዝናብ ሰጭ የሚቲዮሮሎጂ ገጽታዎች መጠናከር ጋር ተያይዞ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል ብለዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች የመሬት መንሸራተት፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ በማሳ ላይ ውሃ የመተኛትና ሰብሉን የማበላሸት ተፅዕኖም ሊያደርስ ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

በአንዳንድ ተፋሰሶች ላይ ከባድ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል በመጠቆምም ሁኔታው በአዎንታዊ ጎኑ የወራጅ ውሃ መጠን ስለሚጨምር ለግድቦችና ለውሃ ማቆሪያ ኩሬዎች ጠቀሜታ ይኖረዋል ነው ያሉት።

ዝናቡ በአርሶና አርብቶ አደር አካባቢዎች ስለሚጨምር የሚገኘውን ውሃ በአግባቡ መጠቀም ይገባል ሲሉም መክረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.