Fana: At a Speed of Life!

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን በመሰለፍ ጠላትን በቁጣ አለንጋ እየገረፍን ነው – የአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ አባላት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ግንባር መዝመታቸውን ተከትሎ በርካታ የወገን ኀይሎች የሞራል ስንቅ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የወገን ኀይሎችና ሕዝቡ ከጎናቸው በመሰለፍ አሸባሪው የትህነግ ወራሪን ለማጥፋት እየተፋለሙ ነው፡፡

አሚኮ ያናገራቸው የአማራ ልዩ ኀይል እና የሚሊሻ አባላት ÷የጀግናው መሪ መዝመት ጠላትን በመደምሰስ ዓላማቸውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሳካት እንደሚያስችላቸው ጠቁመዋል።

ምክትል ኮማንደር በቀለ ጎረምስ ÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ የህልውና አደጋ ውስጥ በመሆኗ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ እስከ ግንባር ድረስ መውረዳቸው የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።

በክፍለ ጦራቸው ውስጥ ከፍተኛ ወኔንና መነቃቃትን መፍጠሩንም ምክትል ኮማንደሩ ጠቁመዋል።

“ለሀገር ሉዓላዊነት እና ክብር ምን ያህል ዋጋ እንደሚሰጠው ከዘማቹ መሪ መማር እንድሚቻል ገልጸው ÷ ክፍለ ጦራችንም ልክ እንደ ተለመደው ጠላትን እየገረፈው ነው” ብለዋል።

ምክትል ኮማንደሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመት የአባቶቻችን የጀግንነት ታሪክ በድጋሜ የታየበት ነውም ብለዋል።

ለዘመቻ ብቁ የሆነ ዜጋ ሁሉ በመዝመት ሀገሩን ከተጋረጠባት አደጋ እንዲታደግ ምክትል ኮማንደር በቀለ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ምክትል ሳጅን ይንገስ ገበየሁ ÷ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመት ጠላትን የሚያስደነግጥ ነው ብለዋል።

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመታቸው ለትግሉ ፍጥነት ወሳኝ ነው፣ ታላቅ አንድምታም ይኖረዋል” ያሉት ኮንስታብል ይንገስ ÷ ሁነቱ ከፍተኛ የሞራል ስንቅ እንደሆነላቸውም ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመት ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካውያን ተምሳሌት ነው ያሉት ደግሞ ኮንስታብል በላይነህ ዋለ ናቸው።

ሁሉም ሕዝብ የሞራል ግዴታ ተሰምቶት እንዲዘምት በር ከፋች መሆኑን ነው የተናገሩት።

ኮንስታብል በላይነህ እንዳሉት ÷ ሁነቱ የወገን ኀይል በሞራልና በአንድነት ሆኖ ጠላት እንዲደመሰስ እያደረገ ይገኛል።

ኮንስታብል ልዑል ጋሻዬ ÷ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመታቸው ሁሉም የመንግሥት ባለሥልጣናት ትኩረታቸውን ወደ ግንባር አድርገው ለመደገፍም ሆነ ለመዝመት ፈር ቀዳጅ ሆኖላቸዋል ብለዋል።

በተለይ በግንባር የሚገኙ የጦር መኮንኖች ግዴታቸውን በብቃት እንዲወጡ ያስችላቸዋልም ነው ያሉት።

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመታቸውን ስሰማ ግርምትን ጭሮብኛል ፤ ጠላትን በጋለ ስሜት እንድቀጠቅጠውም ሞራላዊ ግዴታ በውስጤ አድሯል” ብለዋል።

ከደባርቅ ወረዳ ወደ ግንባር ከዘመቱ የሚሊሻ አባላት ውስጥ አቶ ቢያይልኝ ዓለም የጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመት ሁሉንም የሚያጀግን ነው ብለዋል።

ሁነቱ ጠላት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠፋ ያስችላልም ነው ያሉት።

“የሀገሪቱ ቁንጮ መሪ መዝመታቸው ሁሉም ዜጋ ሰበብ ሳይፈጥር እንዲዘምት ሞራላዊ ጫናን ይፈጥራል” ያሉት አቶ ቢያይልኝ በጋለ ስሜት ሆነው ጠላትን እያስወገዱ እንደሆነ አስረድተዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.