Fana: At a Speed of Life!

ከጤና ተቋማት ውጪ ሞት በሚከሰት ጊዜ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄዎች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከጤና ተቋማት ውጪ ሞት በሚከሰት ጊዜ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የአስከሬን አያያዝ ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሁን ያለው የአስከሬን አቀባበርን አስመልክቶ እንደገለጹት በቀብር ስነ-ስርዓት ወቅት በርካታ ሰዎች ከተለያዩ ቦታዎች ስለሚመጡ የኮሮና ቫይረስን በማስተላለፍ በኩል የተለያዩ አጋጣሚዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ ብለዋል፡፡
ለዚህም ተገቢውን ጥንቃቄ መውሰድ ግድ ሲሆን፥ በዚህም ከጤና ተቋማት ውጪ ሞት በሚከሰትበት ጊዜ ኮቪድ -19ን ለመከላከል የሚደረጉ ጥንቃቄዎች ተከታዮቹ ናቸው።
• ለጤና ተቋም ማሳወቅ እና አስከሬኑ የኮቪድ-19 ላቡራቶሪ ናሙና እንዲወሰድ ማድረግ
አስከሬን የሚገንዙ ሰዎች የእጅ ጓንት፣የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ወይም ከፕላስቲክ የተሰራ ጓንት እና መነጽር እንዲለብሱ ማድረግ
• ሀኪሞች በሌሉባቸው አስከሬን ለማጓጓዝ ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ በሚችሉ ሰዎች ብቻ እንዲከናዎን ማድረግ
• ኮቪድ 19 ምልክት የሚታይባቸው ሰዎች አስከሬን ከሚያጓጉዙ ሰዎች ጋር እንዳይሳተፉ ማድረግ
• በቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ የሚገኙ ሰዎች ሁሉ ሁለት የአዋቂ እርምጃ በመራራቅ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ እንዲሁም አስከሬኑንም ሆነ አስከሬኑ ያለበትን ሳጥን ያለመነካካት፣ በቀብር ስነ-ስርዓቱ ወቅት ከ50 የማይበልጡ ሰዎች መሆናቸውን መከታታል እና ከጤና ተቋማት የሚሰጡ መመሪያዎችን መከታተልና ተግባራዊ ማድረግ
• አስከሬን ከተጫነ በኋላ የሰውነት መከላከያ አልባሳት በመልበስ አስከሬን ያለበትን ሳጥን፣ አስከሬን የገነዙትን ሆነ አስከሬኑ የነካካቸውን ቦታዎች ወይም ቁሳቁሶች፣ ሟቹ የነበረበትን አልጋ፣ የተለያዩ የመገልገያ እቃዎች፣ የቤቱን ወለል፣ የተጓዘበትን መኪና እና አጠቃላይ እቃዎች በበረኪና ውህድ እንዲጸዳ ማድረግ
• አስከሬን የሚያጓጉዙ ሰዎች ጓንት ማድረግ የግድ ሲሆን፥ በጓንታቸው የተለያዩ እቃዎችን ያለመነካካት እና አስከሬኑን ከቦታ ወደ ቦታ አለማንቀሳቀስ
• አስከሬን ከግነዙትም ሆነ ከሟች ቤተሰቦች ሁለት የአዋቂ እርምጃ መራቅ እንዳለ ሆኖ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም
• የሟች ቤተሰቦች በተቻለ መጠን አስከሬኑን በሞተበት አካባቢ መቅበር ይኖርባቸዋል፤ ወደ ሌላ ቦታ የማጓጓዝ ግዴታ በሚፈጠርበት ጊዜ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንደሚኖርበት ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።
• የእምነት ተቋማት ሃላፊዋች እና የሃይማኖት አባቶች አስከሬኑ ወደ ቀብር ቦታ ከመምጣቱ በፊት የኮቪድ-19 የላቦራቶሪ የምርመራ ናሙና መወሰዱን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው።

.

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.