Fana: At a Speed of Life!

ከጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርቶች 140 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ተለያዩ ሃገራት ከተላኩ የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርቶች 140 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ የ2013 በጀት ዓመት የ11 ወር ዕቅድ አፈጸጸሙ ላይ በደብረ ብርሃን ከተማ በተወያየበት ወቅት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ስለሺ ለማ እንዳሉት፤ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ዘርፉን ውጤታማነት ለማስፋፋት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ተገንብተው ወደ ስራ ገብተዋል።

በዘርፉ የተሰማሩ የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ባለፉት 11 ወራት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የፈጠረውን ጫና ተቋቁመው ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ አቅርበው 140 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።

የምርቱ መዳረሻዎች አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ቱርክ፣ ጣልያን እና ጀርመን መሆናቸውን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ÷ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት 90 በመቶ የነበረው የውጭ ገበያ አቅርቦት ወደ 60 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅሰዋል።

የጨርቃ ጨርቅ ዘርፉን በማዘመንና ጥራትን በመጠበቅ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ዘንድሮ በመስኩ ምሁራን 22 ጥናትና ምርምሮች ተደርገው 11ዱ ተጠናቀው ለባለድርሻ አካላት እንዲደርሱ መደረጉን ጠቁመዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ እንዳብራሩት፤ በ2013/2014 የምርት ዘመን የዘርፉን የጥሬ እቃ አቅርቦት እጥረት ለማቃለል በ150 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ 170 ሺህ ቶን ጥሬ ጥጥ ለማምረት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.