Fana: At a Speed of Life!

“ከጳጉሜን እስከ ጳጉሜን እንደርሳለን” በሚል የተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የመንገድ ደህንነት ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)”ከጳጉሜን እስከ ጳጉሜን እንደርሳለን” በሚል የተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የመንገድ ደህንነት ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ፡፡

ንቅናቄው በይፋ በተጀመረበት ወቅት ትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ቀኑ በትራንስፖርት እይታ እና አጠቃቀማችን ላይ ያካሄድ ለውጥ የምንጀምርበት እና ለዜጎች በይበልጥ ፋይዳ እንደሚጨምር የሚጠበቀው የሞተር አልባ ትራንስፖርት በሰፊው ወደ ስራ የምናስገባበት ነው ብለዋል፡፡

ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በሃገራችን ያለው ተሸከርካሪ ቁጥር አነስተኛ ቢሆንም በትራንስፖርት ስርዓቱ ላይ ጫና እያሳደረ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ የመጣውን የመንቀሳቀስ ፍላጎት በማስተናገድ ጥረት ውስጥም የትራንስፖርት ፍላጎት እና አቅርቦት አለመጣጣም፣ከብዙሃን ትራንስፖርቶች ይልቅ የትናንሽ መኪኖች ቁጥር መጨመር፣ የትራንስፖርት ስርዓታችን ከመሬት አጠቃቀማች ጋር አለመጣጣም ይጠቀሳሉ ብለዋል፡፡

ለዚህም ምክንያት መንገዶች ሲገነቡ ለዘመናት ትኩረት የተሰጠው መንገድ ለመኪና የሚለው መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ይህም መቀየር አለበት ያሉት ሚኒስትሯ መንገድ ሁለገብ አገልግሎት መስጫ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

ለዚህም ሚኒስቴሩ ባዘጋጀው የ10 ዓመት የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ የእግረኛ መንገዶችን ማሻሻል ፣የሳይክል መንገዶችን ማሻሻል፤ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ያደረገ የትራንስፖርት አገልግሎትን ማጠናከር እና የመሬት አጠቃቀምን ማሻሻል ይገኝበታል፡፡

የእቅዱ አላማም የአየር ብክለትል መቆጣጠር፣ የእግረኛ፣ የሳይክል እና የህዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን ቁጥር መጨመር፣ የመንገድ ደህንነትን ማሻሻል እና የግል መኪና ተጠቃሚዎችን ቁጥር መቆጣጠር ናቸው ብለዋል፡፡

እቅዱን ወደ ተግባር ለመቀየርም ከህብረተሰቡ ጋር በስፋት ይሰራልም ነው ያሉት፡፡

ይህም የሚያመጣው ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ጥቅሞች ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ተናግረዋል፡፡

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.