Fana: At a Speed of Life!

ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ ነው – የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት የግብርና ስራ ተስተጓጉሎበት የነበረው የደቡብ ወሎ ዞን ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ስንዴ ለማልማት አቅዶ እየሠራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ፡፡
የሽብር ቡድኑ ከአካባቢው በመውጣቱ አርሶ አደሩ ወደ መደበኛ የግብርና ስራ ተመልሷል ፤ በዚህም በዞኑ በ2014 ዓ.ም ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ስንዴ ለማምረት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ ምክትል ሀላፊ አሊ ሰይድ ገልፀዋል፡፡
ተስማሚ የአየር ፀባይ፣ ሰፊ የውሃ አማራጭ፣ በቂ የሰው ሀይልና የተሻለ ድጋፍና ክትትል ታክሎበት እቅዱን ለማሳካት ምቹ ሁኔታ መኖሩን ምክትል መምሪያ ሀላፊው ተናግረዋል፡፡
ደቡብ ወሎ ዞን ባለፈው ዓመት በመስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ አፈፃፀም ያለውና ጥሩ ልምድ የተገኘበት በመሆኑ÷ እቅዱን ለመሸፈን ያስችለናል ማለታቸውን ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለመስኖ ስንዴ ልማት መሬት፣ ውሃና የሚያለማ አርሶ አደር እየተለየ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በዞኑ ለዚህ ተግባር የሚባክን ጊዜ፣ ውሃና ጉልበት እንደማይኖር ከአርሶ አደሩ ጋር መተማመን ያስፈልጋል፤ ለዚህ ደግሞ አመራሩና ባለሙያው በፍጥነት ተልዕኮ ወስዶ ወደ ተጨባጭ ተግባር ሊገባ ይገባል ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.