Fana: At a Speed of Life!

ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የወርቅ ጥፍጥፎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወቅታዊው የገበያ ዋጋ 12 ሚሊየን 350 ሺህ ብር የሚያወጡ እና በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ አምስት የወርቅ ጥፍጥፎች በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
የወርቅ ጥፍጥፎቹ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ማእከል በሰጠው ጥቆማ መሰረት የተገኙ ሲሆን÷ ተጠርጣሪዎቹ ላይም የፌደራል ፖሊስ ምርምራ እያደረገ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እና የሚወጡ የኮንትሮባድ እቃዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሁሉም ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥረት እያደረጉ ሲሆን÷ ለዚህ ስራ ስኬታማነት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ማእከል፣ የፌደራል ፖሊስ ኤርፖርት ዲቪዥን እና የአየር መንገድ ደህንነት መስሪያ ቤት ያበረከቱት አስተዋጥኦ ማበርከታቸው ተመላክቷል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋና ማቅረቡን ከጉሙሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ÷ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል የጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.