Fana: At a Speed of Life!

ከ12 ሺህ በላይ ከድባጤ ወረዳ ተፈናቅለው የነበሩ ነዋሪዎች ወደቀያቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ባከናወናቸው የፀጥታ ስራዎች ተፈናቅለው ከነበሩት የድባጤ ወረዳ ነዋሪዎች መካከል ከ12ሺህ በላይ ወደቀያቸው መመለሳቸው ተገለጸ፡፡

ከህዳር ወር 2013 ዓ/ም ጀምሮ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ወደስራ ማስገባት መቻሉንም የድባጤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉዓለም ዋወያ ተናግረዋል።

ዋና አስተዳዳሪው እንዳሉት ፥ አሸባሪው ህወሓት የጡት አባት ሆኗቸው ስልጠናና ሎጀስቲካዊ አቅርቦትን እየሰጠ ንፁሃን ላይ ጥቃት እንዲፈፅሙ ይልካቸው በነበሩ ሽፍቶችና በሸኔ ላይ ኮማንድ ፖስቱ በወሰደው እርምጃ መሰረት አሁን ላይ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል።

በመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት የድባጤ ወረዳ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ኮለኔል ካሳ ሚደቅሳ ከመከላከያ ሰራዊቱ፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከአማራ ክልል እና ከሲዳማ ክልል ልዩ ኃይሎች እንዲሁም ከድባጤ ወረዳ ሚሊሻ ጋር በጥምረት በመስራት በጠላት ቁጥጥር ስር የነበሩ 17 ቀበሌዎችን ነፃ ማድረግ መቻሉን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.