Fana: At a Speed of Life!

ከ129 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የጎሬ ቦራሌ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በክልሉ የተገነቡ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን መረቁ፡፡
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የውሃ ፕሮጀክቱ ግንባታ በ2011 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን በዋናነት በአካባቢው የሚገኙ ከ57 ሺህ በላይ ዜጎችን እና ከ88 ሺህ በላይ እንስሳትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት መሆኑ በምርቃቱ ወቅት ተገልጿል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ የክልሉ መንግሥት ከለውጡ በኋላ የህዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ በርካታ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው የቀሩትንም በሂደት ለመመለስ ይተጋል ብለዋል።
እንዲሁም በክልሉ በፋፈን ዞን ሸቤለይ ወረዳ የተገነባውን ጤና ጣቢያ መርቀዋል፡፡
ጤና ጣቢያው 32 ሺህ ለሚሆኑ የወረዳው ህዝብና የአጎራባች ወረዳዎች አገልገሎት ይሰጣል ተብሏል።
በዚህ ወቅት አቶ ሙስጠፌ ጤና ጣቢያው ህክምና ለማግኘት ወደ ጅግጅጋ ይመጡ የነበሩ በርካታ ዜጎች በአቅራቢያቸው ህክምና እንዲያገኙ እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡
ባለፉት ሶስት አመታት በክልሉ በ441 ሚሊየን ብር ወጪ 49 ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም በ 1 ቢሊየን ብር ወጪ 11 ሆስፒታሎች መገንባታቸውንም ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ በዚሁ ዞን ከ8 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የአነኔ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትንም መርቀው ከፍተዋል፡፡
የግንባታውን ወጪው በሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ መሸፈኑ ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.